Talk:Geze Gofa

Page contents not supported in other languages.
From Wikipedia, the free encyclopedia

የጎፋ ዞን የገዜ ጎፋ ወረዳ gofa zone geze gofa woreda[edit]

የጎፋ ዞን በክልሉ ካሉ 17 ዞኖች አንዱ ሲሆን አጠቃላይ ቆዳ ስፋቷም 4551 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ነው፡፡ የዞኑ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ 5054’N -- 6044’N ላቲትዩድ እና 36020’E-- 37020’E ሎንጊቱድ ነው፡፡ በሰሜን ከዳውሮ ዞንና ኮንታ ልዩ ወረዳ፣ በደቡብ ከደቡብ ኦሞ ዞንና ጋሞ ዞን፣ በምስራቅ ከዳውሮ ዞንና ጋሞ ዞን፣ በምዕራብ ከደቡብ ኦሞ ዞንና ባስኬቶ ልዩ ወረዳ ጋር ይዋሰናል፡፡ የዞኑ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ 5054’N -- 6044’N ላቲትዩድ እና 36020’E-- 37020’E ሎንጊቱድ ነው፡፡ በሰሜን ከዳውሮ ዞንና ኮንታ ልዩ ወረዳ፣ በደቡብ ከደቡብ ኦሞ ዞንና ጋሞ ዞን፣ በምስራቅ ከዳውሮ ዞንና ጋሞ ዞን፣ በምዕራብ ከደቡብ ኦሞ ዞንና ባስኬቶ ልዩ ወረዳ ጋር ይዋሰናል፡፡ የገዜ ጎፋ ወረዳ በዞኑ ወስጥ ካሉት 7 ወረዳዎችና 4 ከተማ አስተዳደሮች ዉስጥ አንዱ ሲሆን አጠቃላይ ቆዳ ስፋቷም 79508 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ነው፡፡ የወረዳዉ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ 6150’N 6320’N ላቲትዩድ እና 36400’E 37350’E ሎንጊቱድ ነው፡፡ በሰሜን መሎ ኮዛ ፣ በደቡብ ኦይዳ፣ በምስራቅ ደምባ ጎፋ፣ በምዕራብ ባስኬቶ ጋር ይዋሰናል፡፡ የወረዳዉ ዋና ከተማ ቡልቂ ሲሆን ከአዲስ አበባ በ543 ኪሎ ሜትር፣ ከክልሉ ርዕሰ ከተማ አዋሣ 317 ኪሎ ሜትር፣ ከዞን ዋና ከተማ ሳዉላ 17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ አጠቃላይ የህዝብ ብዛትም 83435 ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ 80% ህዝብ በገጠር የሚኖርና 80 % የሚሆነው በእርሻ ሥራ የሚተዳደር ነው፡፡ ቀሪው የህብረተሰብ ክፍል በንግድ ሥራና በአነስተኛና ጥቃቅን የሥራ ዘርፎች ተደራጅቶ የሚሠራ ነው፡፡ የወረዳዉ የአየር ንብረት በሶስት የተከፈለ ሲሆን ደጋ 20.5%፣ ወይና ደጋ 67%፣ ቆላ 12.5% ነው፡፡ የመሬት አቀ ማመጡም ሜዳማ፣ወጣ ገባና ሰንሰለታማ ተራሮችን ያቀፈ ነው፡፡ የወረዳዉ አየር ንብረትና የመሬት አቀማመጥ በጣም ማራኪና ለእርሻ ሥራ፣ለኢንቨስትመንት፣ ለቱሪዝም ክፍለ ኢኮኖሚና ለኑሮ ምቹ የሆነ ነው፡፡ የወረዳዉ የመሬት አቀማመጥ ከባህር ጠለል በላይ በአማካይ 2400 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን በወረዳዉ በከፍታቸው የታወቁ 2700 ሜትር ከፍታ ያለው ባይጻ ተራራ ሜትር ከፍታ ያለው ተራራ ናቸው፡፡ የወረዳዉ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን 1500 ሚ.ሜትር ነው፡፡ የወረዳዉ ፓለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ገፅታን በተመለከተ የገዜ ጎፋ ወረዳ ምቹና አሳታፊ የፖለቲካ አደረጃጀት ያለበት ወረዳ ሲሆን ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ልዩ ትኩረት የተሰጠበትና ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች በእኩል እየተስተናገዱ ያሉበት ወረዳ ነው፡፡ የገዜ ጎፋ ወረዳ ለአስተዳደራዊ አመቺነት በ28 ቀቤለዎችና በ5 ማዘጋጃ ቀበሌዎች የተከፋፈለ ነው፡፡ በወረዳ ያልተማከለ አስተዳደር ሥርዓት ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ህዝቡም ከቀበሌ እስከ ፌደራል ባሉ መንግስታዊ የአስተዳደር እርከኖች በተወካዮቹና በቀጥታ በውሳኔ ሰጪነት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡ በወረዳ በመንግስት ሥራ ላይ የተሠማራ የሰው ኃይል ብዛት ወንድ 1363 ሴት 507 ድምር 1870 ነው፡፡ የወረዳ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታን በተመለከተ የወረዳዉ አጠቃላይ ማክሮ ኢኮኖሚ በእርሻ ሥራ፣ጥቃቅንና አነስተኛ የማምረቻ ዘርፍና በንግድ ሥራ ገቢ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ከአጠቃላይ የመሬት መጠን በእርሻ ሥራ የለማ መሬት 37569.57 ሄክታር 47.25 %፣ የሚለማ መሬት 2743.5 ሄክታር 3.45 %፣ለግጦሽ የዋለ መሬት 1136.25 %፣በውሃ የተሸፈነ መሬት 115.35 ሄክታር 0.145%፣በደን የተሸፈነ መሬት 17938.87 ሄክታር 22.56%፣ በሌሎች የተሸፈነ መሬት መጠን 20004.5 ሄክታር 25.16% ነው፡፡ በወረዳ የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት መብት ለማረጋገጥ በተካሄደ የመሬት ልኬት መሠረት 45100 አርሶ አደሮች የመሬት ማረጋገጫ ደብተር ተሰጥቷቸዋል፡፡ ወረዳዉ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ክፍለ ኢኮኖሚ ምቹ የአየር ንብረትና መሬት ያለው ሲሆን በወረዳዉ 208 ሄክታር መሬት ለኢንቨስትመንት ሥራ ተዘጋጅቶ ይገኛል፡፡ የቱሪስት መስዕብን በተመለከተ የወረዳዉ ህዝብ ቱባ ባህላዊ ቅርሳቅርሶችና ድንቅ ዋሻዎችና ብርቅዬ አራዊት ያሉበት ሻች ፓርክ እና ሌሎች ተፈጥሮአዊ የመስዕብ ቦታዎች የሚገኙበት ወረዳ ነው፡፡ የእርሻ ሥራ በዋነኛነት የሚካሄደው በዝናብና በአነስተኛ የመስኖ ሥራ ሲሆን በወረዳዉ በአነስተኛ መስኖ የለማ መሬት 1447.5 ሄክታር ነው፡፡ ይህም በእርሻ ሥራ ከለማው መሬት 3.85% ነው፡፡ የወረዳዉ ዋና ዋና ምርት የሰብል፣ ቅመማቅመም ፣ፍራፍሬና ከብት እርባታ ነው፡፡ የሰብል ምርቶችን በተመለከተ ቦቆሎ፣ጤፍ፣ስንዴ፣ገብስ ባቄላ፣አተር ቦሎቄ ሲሆኑ፤ የቡናና የቅመማቅመም ምርቶች ቡና፣ ኮረሪማና ዝንጅብል ናቸው፡፡ የቅባት እህሎች ሰሊጥና ኦቾሎኒ ሲሆኑ ፍራፍሬን በተመለከተ ሙዝ፣ማንጎ አቮካዶ፣ብርቱካን ሎሚ ይመረታል፤ ከሥራ ስር ምርቶች ነጭና ቀይ ሽንኩርት፣ ካሳቫ ይመረታል፡፡ ቡናና ሰሊጥ ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ሲሆኑ ቦቆሎ፣ጤፍ፣ገብስ ስንዴ፣ሙዝ ማንጎ፣ ካሳቫ በከፍተኛ ደረጃ ተመርቶ በበቂ ደረጃ ለአገር ውስጥ ገበያዎች ፍጆታ የሚቀርቡ ምርቶች ናቸው፡፡ በገዝ ጎፋ ወረዳ የእንስሳት እርባታና ልማት በከፍተኛ ደረጃ የሚካሄድ ሲሆን የቀንድ ከብቶች ላም፣በሬ፣በግ፣ፍየል በአርሶ አደር ደረጃና በተደራጁ ማህበራት አማካይነት እርባታና የማድለብ ሥራ የሚካሄድ ሲሆን፤ የደለቡ ከብቶች በሬ፣በግ፣ፍየል በከፍተኛ ደረጃ ለአገር ውስጥና ለውጪ ገበያም ጭምር በጥራትና በብዛት በመቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሠረት መንግስት የአቅርቦት አቅምን ለማሳደግ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የቀንድ ከብት ፍየሎችና በጎች፣ የጋማ ከብት መገበያያ ማዕከል በቡልቂ ከተማ በ--------------- ካሬ ሜትር ላይ ተገንብቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የማህበራዊ አገልግሎትን በተመለከተ በወረዳዉ የጤና ሽፋንን ለማሳደግ 5 ጤና ጣቢያዎች እና ---------- ጤና ኬላዎች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፤ የትምህርት ሽፋንን በተመለከተ 44 ቅድመ መደበኛ ት/ቤቶች፣ 44 ሙሉ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣4 ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በወረዳዉ የትምህርትና ስልጠና ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡ የመንገድ ልማትና አገልግሎትን በተመለከተ በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ሥራ ፕሮግራምና በህዝብ ተሳትፎ ቀበሌ ከቀበሌ እና ቀበሌን ከወረዳ ጋር የሚያገናኙ የጠጠር መንገዶች ግንባታና ሽፋንን በተመለከተ ------------ ኪሎ ሜትር የበጋ የጠጠር መንገድ የተገነባ ሲሆን ይህም ከወረዳዉ የቀበሌያት ብዛትና አቀማመጥ አንፃር ሲታይ በጣም አነስተኛ ሽፋን ነው፡፡ ከሣውላ እስከ ቡልቂ 17 ኪ.ሜትር አስፓልት መንገድ ተገንብቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የወረዳዉ አጠቃላይ የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ከአጠቃላይ የወረዳዉ ህዝብ ተጠቃሚነት አንፃር ሲሰላ 39.9 % ነው፡፡ በወረዳዉ የዘመናዊ ስልክ አገልግሎትና የዲጂታል ፋይቨር ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚነትን በተመለከተ በቡልቂ ከተማ አሰ/ር ቢቻ የሚገኝ ሲሆን በገጠር ------------ ቀበሌያት የስልክ ተጠቃሚ ሆኗል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል በወረዳዉ ዋና ከተማ የ24 ሰዓት ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች ሲሆኑ በወረዳዉ ውስጥ ካሉ 33 የማዘጋጃና የገጠር ቀበሊያት ውስጥ 3 ቀበሌያት የመብራት አግልግሎት ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ይህም ሽፋን -----------% ነው፡፡ Animut geremew (talk) 09:22, 25 August 2022 (UTC)[reply]

የጎፋ ዞን ጎፋ ወረዳ ዌብሳይት gofa zone geze gofa woreda website[edit]

. Animut geremew (talk) 09:27, 25 August 2022 (UTC)[reply]